ለተማሪዎች ሰርቪስ በተሰማሩ ተሸከርካሪዎች ላይ አራት እጥፍ የታሪፍ ጭማሪ መደረጉ ቅሬታ አስነሳ፡፡

የሸገር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በተማሪ ሰርቪስ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ የተማሪ ወላጆች ከፍተኛ ቅሬታ እሰሙ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም ከተማሪ ወላጆች እንዳረጋገጠዉ፣ከዚህ በፊት ይከፍሉት ከነበረው ታሪፍ ላይ አራት እጥፍ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል፡፡

ወላጆች ከዚህ በፊት 450 ብር በየወሩ ይከፍሉ የነበረ ሲሆን አሁን ባለው መሰረት 1ሺህ 870 ብር እንዲከፍሉ ተገደዋል፡፡
በዚህም የተማሪ ወላጆች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ወላጆች ለጣበያችን እንደተናገሩት፣ መንግስት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከታተሉ እያደረገ ባለበት በዚህ ሰአት ይህ መደረጉ አግባብነት የለውም፡፡
“እኛ እንደወላጅ ከመንግስት የመጣ ሃሳብ ነው አንልም፣ ዜጎች በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዲያድርባቸው በሚያደርጉ አካላት የተፈጠረ ሊሆን ይችላል ብለዋል”፡፡
ወላጆች ዝቅተኛው ኪሎ ሜትር 250 ብር በየወሩ የሚከፍሉ ሰሆን ከፍተኛው ደግሞ 3 ሺህ 110 ብር እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡

አሁን ወላጆች ለልጆቻችን ለትራንስፖርት የምንከፍለው እና የምናገኝው ገቢ ተመጣጣኝ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም ይህንን ገዳይ በተመለከተ የሸገር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሃላፊዎችን ለማነጋግር በአካል ቢሯቸዉ ድረስ ብንሄድም ስብሰባ ናቸዉ በሚል ልናገኛቸዉ አልቻልንም፡፡

ሆኖም ደርጅቱ ለወላጆች በጻፈው ደብዳቤ መሰረት እስከ ህዳር 15 ቀን 2015 አመት ድረስ በተመዘገቡበት አካባቢ ሄደዉ ውላቸውን እንዲያድሱ ጠይቋል፡፡

ውላቸውን እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ካላደሱ የማይስተናገዱ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.