ተቋርጦ የነበረው ዋትስአፕ መተግበሪያ ወደ አገልግሎት ተመለሰ

በመላው ዓለም ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው ዋትስአፕ መተግበሪያ ወደ አገልግሎት ተመለሰ።

ዋትስ አፕ መተግበሪያ የሜታ ኩባንያ ንብረት ሲሆን በዓለም ደረጃ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት አቁሞ እንደነበረ ድርጅቱ አስታውቋል።

መተግበሪያው አገልግሎት መስጠት ያቆመው ዋትስአፕ ኩባንያ በአሮጌ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ እንዳይሰራ ከተደረገ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

በኢትዮጵያም ይህ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን በርካታ የመተግበሪያው ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ መቋረጡን በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ ሲያጋሩ ቆይተዋል።

የሜታ ኩባያም ዋትስአፕ በዛሬው ዕለት ያጋጠመው የአገልግሎት መቋረጥ የቴክኒክ ችግር መሆኑን አስታውቆ፤ ከሰዓታት በኋላ ወደ አገልግሎት መመለሱን ገልጿል።

ዋትስ አፕ ከዚህ በፊት ባወጣው መግለጫ በፈረንጆቹ ከጥቅምት 24 ቀን 2022 ጀምሮ በአይፎን ስልኮች ላይ አይኦኤስ 10 እና 11 ወይም አይፎን 5ኤስ፣ አይፎን 6 እንዲሁም አይፎን 6ኤስ ስልኮች ላይ አገልግሎቱ እክል እንደሚገጥመው አስታውቆ ነበር።

ዋትስ አፕ መተግበሪያ በዓለማችን ሁለት ቢሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ብዙ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይገለጻል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *