ፈተናዉን አቋርጠዉ የወጡ ተማሪዎች በድጋሚ አይፈተኑም!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አቋርጠዉ የወጡ ተማሪዎች በድጋሚ ፈተናዉን እንደማይወስዱ ትምህርት ሚንስቴር በድጋሚ አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሚንስትሩ በዚሁ መግለጫቸዉ ላይ እንደተናገሩት በፈተናዉ ሂደት በአጠቃላይ 12 ሽህ 993 ተማሪዎች ፈተናዉን አቋርጠዉ ወጥተዋል፡፡
እነዚህን ተማሪዎች የመፈተን እቅድ እንደሌለዉ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረዉ የድልድይ መደርመስ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸዉና በፈተናዉ ወቅት የወለዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ፈተናዉን እንደሚወስዱ ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡

ለፈተናዉ ዝግጁ ከነበሩ አጠቃላይ ተማሪዎች 98 በመቶ የሚሆኑት ፈተናዉን በአግባቡ መዉሰዳቸዉን የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በየትኛዉም ዩኒቨርሲቲ አንድም የትምህርት አይነት እንዳልተሰረቀ አረጋግጠዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.