ከ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ገንዘብ በመሰብሰብ የፈተና መልስ ሰጥተዋል የተባሉ ርዕሰ መምህሩን ጨምሮ 5 መምህራን ተከሰሱ፡፡

ክስ የተመሰረተው አንደኛ ርዕሰ መምህር አብዱ ሸኩር ጀማል፣ ሁለተኛ ተከሳሽ የድሬዳዋ ፖሊስ ዋና ሳጅን አብዲ ዩያ ፣ ሶስተኛ መምህር መሃመድ ጠሃ አብዱላሂ እና አራተኛ መምህር ማሙሽ አካሉ ተክሌ፣ እንዲሁም አምስተኛ መምህር ሲሳይ ደስታ ሚጆና ላይ ነው ተብሏል፡፡

ለተማሪዎቹ የባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ የህብረተሰብ ሳይንስ እና የስነ-ዜጋ የትምህርት አይነቶችን ፈተና መልስ በማለት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች እየዞሩ ተማሪዎቹ እንዲሞሉ ያደረጉ ሲሆን ዉጤት ይፋ ሲደረግ ሁሉም ተማሪዎች ከማለፊያ ነጥብ በታች ማምጣታቸው ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑ ተከሳሾች በፈፀሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

ክሱ ለተከሳሾች የደረሳቸው ሲሆን የድሬዳዋ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሳሾች ከጠበቃ ጋር ተማክረዉ ለመቅረብ በጠየቁት መሰረት ለጥቅምት 22/2015 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *