ሩሲያ በቅርቡ ከዩክሬን ከወሰደቻቸዉ አራት ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችዉ በዣፓርዢያ ግዛት ዉስጥ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በሚያሰራጩ ሰዎች ላይ የሞባይል ስልክ ፍተሻ መጀመሯን አስታዉቃለች፡፡
በሩሲያ የክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት ቮሎድሚር ሮጎቭ በግዛቷ ዉስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የሞባይል ስልክ ፍተሻ መጀመሩን በቴሌግራም ገጻቸዉ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡
ቮሎድሚር ሮጎቭ በፍተሻዉ ወቅት ማንኛዉም ለአሸባሪዉ የዩክሬን መንግስት የዉጭ ተላላኪ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ በወንጀል ሊከሰስ እንደሚችል ማስታወቃቸዉን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በቤዛዊት አራጌ
ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም











