ዳሽን ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 117 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ

የዳሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር 29ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን የአውሮፓዊያኑ 2021/22 የሂሳብ ዓመት አፈፃፀምን የተመለከቱ ሪፖርቶች ቀርበው ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ዱላ መኮንን እንደገለጹት ምንም እንኳን ተግዳሮቶች የነበሩ ቢሆንም ባንኩ በ20201/22 የሂሳብ ዓመት መልካም አፈጻጸም አስመዝግቧል።

በዚህም የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 117 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ24 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

የባንኩ ባለአክሲዮኖች ድርሻም ወደ 14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ሲሆን ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ42 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። ባለአክሲዮኖቹ ባለፈው ጉባኤያቸው ተጨማሪ ካፒታል ለማቅረብ መወሰናቸውን ተከትሎ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል መጠንም 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 17ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.