የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ራማፎሳ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአሜሪካ መንግሥት ከሀገራቸው ጋር ምንም መረጃ ሳይለዋወጥ የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን አሳዛኝ ብለውታል።
የመግለጫውን መውጣት ተከትሎም ስጋቱ ከየት የመጣ ነው የሚለውን ለማጣራት ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ ውይይት ማካሄዳቸውን፤ ይህንንም በማጣራት ሂደት ላይ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
እንዲህ ያሉ ማስጠንቀቂያዎች በህዝቡ ላይ ከባድ ድንጋጤን የሚያስከትሉ መሆናቸውን
አንስተዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካውያን ይህን መሰሉን መረጃ በራሳቸው በደቡብ አፍሪካ መንግሥት ሊነገራቸው እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሀገሪቱ ተቋማት የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ በተሻለ ቁመና ላይ ናቸው ያሉት ፕሬዝደንቱ እንዲህ ያለውን ስጋት በንቃት እየተከታተሉ መሆኑንና ይህንኑ ማድረግም እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።
በ ትናትናዉ ዕለት በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ ኤምባሲ በተለይ ጆሃንሰበርግ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር።
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም











