ኦባሳንጆ መግለጫ ይሰጣሉ!

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ንግግር ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለሥልጣናት ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ካለፈው ሳምንት አንስቶ ስላካሄዱት የሰላም ንግግር ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጡ ደቡብ አፍሪቃ ማስታወቋን የDW ዘገባ ያመለክታል።

የደቡብ አፍሪቃ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሰላም ንግግሩን የሚመሩት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ የኢትዮጵያውን ግጭት ለመፍታት በአፍሪቃ ኅብረት ስለሚመራው የሰላም ንግግር ዛሬ ለመገናኛ ብዙሀን ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አንድ ለሰላም ንግግሩ ቅርበት አለው ያለውን ከትግራይ በኩል ያገኘውን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው ንግግሩ ከአንዳንድ ለውጦች ጋር ዛሬ ረቡዕ ይጠናቀቃል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ለሲጂ ቲኤን መግለጫ ከሰላም ንግግሩ ጋር በተገናኘ «በርካታ ጣልቃ ገብነቶች» መኖራቸውን መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.