በእስራኤል ምርጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፓርቲ አሸነፈ፡፡

በሀገረ እስራኤል በተካሄደ ጠቅላላ ምርጫ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያን ኔታንያሁ የሚመራው ጥምር ፓርቲ ማሸነፉ ተረጋግጧል።
በዚህም ቀኝ ዘመሙ የፖለቲካ ፓርቲ ከ120 የእስራዔል ክኔስት መቀመጫ 64 ማግኘት ችሏል፡፡

ይህም የቀድሞዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ ዳግም እስራኤልን ለመምራት ዕድል የሠጠ ነዉ ተብሏል፡፡
የወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የር ላፒድ ኔታንያሁንን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢስሃቅ ሄርዞግ ለቤንያሚን ኔታንያሁ መንግስት እንዲመሰረቱ እድል ከሰጡ በኋላ ኔታንያሁ በ28 ቀናት ዉስጥ መንግስት ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

ቤንያሚን ኔታንያሁ በሙስና ቅሌት ተጠርጥረዉ ክሳቸዉ በሂደት ላይ እንደሚገኝ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.