የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በነገው ዕለት በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ ታዉቋል፡፡
በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸዉን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታዉቀዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የስምምነት ሂደቱን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም











