8ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ሳምንት እና 6ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ኮንፈረንስ ሊከበር ነው።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ መሀንዲሶች የሚካፈሉበት ይህ ፕሮግራም፣ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንደገለፁት፣ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ20 በላይ የተለያዩ የጥናት ፅሁፎች ከሀገራችን እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች ይቀርባሉ።

ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ይህ ዝግጅት፣ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መክፈቻውንም በሳይንስ ሙዚየም ያደርጋል ነው ያሉት።

ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓለም ኢንጂነሪንግ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኮንፍረንሱ ፕሬዝዳንት የተገኙ ሲሆን “ሁሌም ለአፍሪካ የሌላ ሀገር መሀንዲሶች መንገዱን ፣ ህንፃውን መስራት የለባቸውም፤ይህ ቀጣይነት የለውም፣በእኛው በራሳችን መስራት አለብን፤ እንችላለንም ” ሲሉ ገልጸዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት የሪል ስቴት አልሚ ተቋማት ፣ የሊዝ አገልግሎት ሰጪዎች ፣ የሀገራት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፉ መምህራን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
መሪ ቃሉም “የአፍሪካን የመሠረተ ልማት ዕድገት በጋራ እናፋጥን” የሚል መሆኑንም ለማወቅ ችለናል።

በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.