የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኗል።
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከዚህ ቀደም በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲወጣ የፈቀደለት ቢሆንም፤ ዐቃቤ ህግ በውሳኔው ቅር መሰኘቱን በመግለጽ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ መጠየቁ ይታወሳል።
በዚህም በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 3 ተደራራቢ ክሶች ስለቀረቡበት ፍ/ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል በማለት ሂደቱ እንዲቀጥል ያዘዘ ሲሆን፤ ጥቅምት 30/2015 ፍ/ቤት ቀርቦ መዝገቡ ለውሳኔ በሚል ለዛሬ ህዳር 1/2015 መቀጠሩ አይዘነጋም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 01 ቀን 2015 ዓ.ም











