የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን ተናገረ።

አስተዳደሩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለተቋራጮች መክፈል የነበረበትን 10 ቢሊዮን ብር መክፈል ባለመቻሉ፣ ተቋራጮች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን እንዳቋረጡ ሪፖርተር ዘግቧል።

ከ200 የፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች መካከል፣ 60 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በጸጥታ መጓደል ሳቢያ እንደተቋረጡ አስተዳደሩ መግለጹን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል።

አስተዳደሩ ይህን የገለጸው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።

ህዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.