ሕብረት ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በጋራ ለመስራት በዛሬዉ እለት ተፈራርሟል።

ሕብረት ባንክ “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አገልግሎት ለማስጀመር ነው ከማስተር ካርድ ስምምነት የተፈራረመው።

“ሕብር ኢ-ኮሜርስ” በኢትዮጵያ የሚሰሩ የንግድ ድርጅቶች በኦንላይን ለሸጡት እቃ ክፍያ በአለም አቀፍ የካርድ ክፍያ መንገዶች መቀበል የሚያስችላቸው የዲጂታል ፕላትፎርም መሆኑ ነው የተገለፀው።


በማስተር ካርድ የክፍያ ጌትዌይ አማካኝነት የሚሰራው “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ተቋማትና ነጋዴዎች በማስተር ካርድና በሌሎች አለምአቀፍ ተቀባይነት ባላቸው ካርዶች ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ ደንበኞች መቀበል እንዲችሉ የሚረዳ ነው ተብሏል።


የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ይህ የክፍያ አገልግሎት ቪዛንም ማስተርካድንም የሚቀበል መሆኑን ገልፀው፣ በአለምአቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ወደ 3 ቢሊየን የሚጠጉ የካርድ ተጠቃሚዎች ጋር የሚያገናኝ ነው ብለዋል።

ይህ የክፍያ አገልግሎት ሻጮች ለሸጡት ምርት ክፍያቸውን በውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን፣ የሀገራችን የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲያድግም አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲሉ አክለዋል።

ከ24 አመት በፊት የተመሠረተው ሕብረት ባንክ በሳይበር ደህንነት የISO 27001 ተሸላሚ ባንክ ነው።

በእስከዳር ግርማ
ህዳር 05 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.