በአዲስ አበባ በ48 ወረዳዎች ላይ የኤች አይቪ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

በኢትዮጵያ ስርጭቱ ቀንሶ እንደነበር የሚነገረዉ የኤች አይ ቪ ስርጭት አሁን ላይ እየተባባሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው በመዲናዋ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን 3 ከመቶ መድረሱን አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የከተማው ጤና ቢሮ በጋራ ባስጠኑት ጥናት መሰረት በመዲናዋ 48 ወረዳዎች ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም በመዲናዋ 50 ወረዳዎች ደግሞ መካከለኛ የኤች አይቪ ስርጭት መኖሩ የተነገረ ሲሆን በ20 ወረዳዎች ደግሞ የስርጭት መጠኑ ዝቅተኛ መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆነባቸው ክፍለ ከተሞች መካከል አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀዳሚነት የተቀመጠ ሲሆን፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አራዳ እንዲሁም ቦሌ ክፍለ ከተሞች ላይ ስርጭቱ እያየለ ይገኛል ሲል ጤና ቢሮው አስታውቋል፡፡

ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ መበራከታቸው ለስርጭቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ የተነገረ ሲሆን በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት መጠኑ 23 ከመቶ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ከሴተኛ አዳሪዎች በተጨማሪም የህግ ታራሚዎች 4 ከመቶ የስርጭት መጠን እንደሚሸፍኑ ተነግሯል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ህዳር 07 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.