የፍትህ መፅሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳላኝ በ30 ሺሕ ብር ዋስትና በዛሬዉ ዕለት ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ችሎት ትላንት ኀዳር 6 ቀን 2015 በዋለዉ ችሎት ጋዜጠኛው በ30 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም የቂልንጦ ማረሚያ ቤት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ማደሩ ይታወቃል።

ዛሬ ኀዳር 7 ቀን 2015 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ176 ቀናት የእስር ቆይታ በሗላ መፈታቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 07 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *