የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ የመንግስትን ወርሃዊ ኪሳራ ከ10 ቢሊዮን ብር ወደ 4 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረጉ ተነገረ፡፡

የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ የመንግስትን ወርሃዊ ኪሳራ ከ10 ቢሊዮን ወደ 4 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረጉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቋል፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተጣለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ከሶስት ወራት በፊት ተግባራዊ የሆነው የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ በዘርፉ እምርታ እያመጣ ነው።

ለአብነትም መንግስት በየወሩ በነዳጅ ድጎማ ይደርስበት የነበረውን ኪሳራ ከ10 ቢሊዮን ወደ 4 ቢሊየን ብር መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል።

መንግስት እስካሁን በነዳጅ ድጎማ 179 ቢሊዮን ብር ዕዳ ወይም ኪሳራ እንዳለበት ጠቅሰው፤ የድጎማው ሂደቶች እየተስተካከሉ ሲመጡ ቀስ በቀስ ዕዳውን መቀነስ ያስችለዋል ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.