ላየን ኢትዮጵያ ሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ኮሌጅ ከ3 መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል

ኮሌጁ በሆቴል፣ በቱሪዝምና ቢዝነስ የትምህርት ምስኮች ያሰለጠናቸውን 3 መቶ 11 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል ።

የኮሌጁ ባለቤት አቶ ሙሃመድ አወል ላየን ኢትዮጵያ የሆቴል፣ቱሪዝምና ቢዝነስ ኮሌጅ ላለፉት 20 ዓመታት ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉን አንስተዋል።

በቀጣይም የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ደስታ ሎሬንሶ በበኩላቸው ለቱሪዝም ዕድገት ብቁና የሰለጠነ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

አዲስ አበባ ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ዕውን ለማድረግ የማሰልጠኛ ተቋማቱ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል

ላየን ኢትዮጵያ የሆቴል ፣የቱሪዝምና የቢዝነስ ኮሌጅ ከተመሠረተ 20 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዛሬ ያስመረቀው ለ19ኛ ዙር መሆኑ ታውቋል።

ኮሌጁ ባለፉት አመታት ከ10 ሺህ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቁን የገለፀ ሲሆን ከፍለው መማር ለማይችሉም ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አስታውቋል ።

በአባቱ መረቀ
ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.