ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ የሰው ህይወት ቀጠፈ

ትላንት ማክሰኞ ምሽት 2:08 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታዉ ጨፌ ስላሴ አየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሶሰትና የአራት ዓመት አድሜ ያላቸዉ ሁለት ህጻናት ህይወታቸዉ ሲያልፍ አንድ የሰባት አመት ታዳጊ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

ሁኔታዉ እንዲህ ነዉ። የህጻናቶቹ እናት በመኖሪያ አካባቢዋ በሚገኝ አንድ ፋብሪካ ዉስጥ ሰራተኛ ናት ። አደጋዉ በደረሰበት ምሽትም ለስራ ወደፋብሪካዉ በሄደችበት ጊዜም ሶስት ልጆች እቤት እንዳሉ በር ከዉጭ ቆልፋባቸዋለች ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በአካባቢዉ በአጋጣሚ ኤሌክትሪክ ኃይል ስላልነበረ በቤት ዉስጥ ሻማ ተለኩሶ ነበር ።

ሳይጠፋ የተዘነጋዉ ሻማ ተቀጣጥሎና ተስፋፎቶ ህጻናቱ በተኙበት ህይወታቸዉ እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸዉ ደህንነት በማሰብ በልጆች ላይ በር መቆለፍን እንደመፍትሄ እየወሰዱ ይገኛሉ ።

ነገር ግን እንዲህ ዓይነት አደጋ ሲያጋጥም ጸጸቱ ከባድ በመሆኑ ሌሎች አማራጮችን ማስተዋል ያስፈልጋል። ሌላዉ የሻማ ብርሀን አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ባለመረዳት በህብረተሰባችን ዘንድ መዘናጋት ይታያል።

ነገር ግን ሻማ ተገቢዉ ጥንቃቄ ካልተደረገበት እንዲህ ዓይነት አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት እድል ሰፊ ነዉ። በተለኮሰ ሻማ በተፈጠረ መዘናጋት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ንብረትም ወድሟል።ስለሆነም ሻማ ለኩሰን ከቤት መዉጣት ወይም ሳያጠፉ መተኛት አደገኛ ነዉ ። ዘገባው የእሳት ና ድንገተኛ ነው።

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.