እስራኤል፣አሜሪካ ኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንትወስድ ጠየቀች፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሓይል ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቪቭ ኮቻቪ አሜሪካ ኢራንን እንዴት ማጥቃት እንዳለባት አዲስ አቅድ ልታወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
ኮቻቪ የአሜሪካ ጦር በፍጥነት የኢራንን ጉዞ ለመግታት እርምጃ እንዲወሰድም አሳስበዋል፡፡

የእስራኤል የጦር አመራሩ ከአሜሪካ አቻቸዉ ማርክ ሚሌ ከአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪዉ ጃኪ ሱሊቫንና ከሲ አይ ኤ ዋና ዳይሬከተር ዊሊያም በርንስ ጋር በጉዳዩ ላይ መምከራቸዉንም የእስራኤል መካከላከያ ሓይል አስታዉቋል፡፡

የሁለቱ አገራት የደህንነት አመራሮች የኢራን የኒውክሌር እንቅስቃሴን ለመግታት ስምምነት ላይ መድረሳቸዉንም ቴል አቪቭ አስታዉቃለች፡፡

የአሜሪካዉ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪዉ ጃኪ ሱሊቫንም ኢራን በምንም አይነት መንገድ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን አንድታነግብ አንፈቅድላትም፣ለዚህም አስፈላጊዉን እረምጃ እንወስዳለን ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

የእስራኤል የደህንነት ሰዎች እንደሚሉት እርግጠኖች ነን ኢራን አዉዳሚዉን የኒውክሌር ቦምብ ለመታጠቅ ተቃርባለች ብለዋል፡፡
ኢራን በበኩሏ ክሱ መሰረተ ቢስ ነዉ ስትል አጣጥለዋለች፡፡

በአባቱ መረቀ
ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.