የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህክምና መሳሪያዎችን አጓጓዘ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእርዳታ የተገኙ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን ከፈረንሳይ ወደ ኢትዮጵያ አጓጓዘ፡፡

አየር መንገዱ ከኤርባስ ፋዉንዴሽን እና አቪዬሽን ሳንፍሮንቴርስ የተገኙ 10ቶን የሚመዝኑ የህክምና መሳሪያዎች አዲስ በተረከበዉ ኤርባስ 350 የመንገደኞች አዉሮፕላን በማጓጓዝ ለጤና ሚኒስቴር በዛሬዉ ዕለት አስረክቧል፡፡

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓላማዎቹ አንዱ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያን ፋዉንዴሽን የሚል አቋቁመን ከጤና ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ነን፡፡

ከኤርባስ ፋዉንዴሽን ፣ ከቦይንግ ጋር እንሰራለን፡፡›› ያሉት አቶ መስፍን አየርመንገዱ በቅርቡ በሚረከባቸዉ ሶስት ቦይንግ 737 ማክስ አዉሮፕላኖች ሌሎች የህክምና መርጃ መሳሪያዎች እንደሚያጓጉዝ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ ዋነኛ አጋራችን ነዉ ››ብለዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተከሰተ እና በሌሎችም አገራዊ ችግሮች ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ የህክምና መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶች በማጓጓዝ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ያስታወሱት ዶ/ር ሊያ በአሁኑ ወቅትም በግጭት የወደሙ የህክምና ተቋማትን መልሶ በመገንባት እና በማጠናከር አየርመንገዱ የህክምና መሳሪያዎችን በነጻ በማጓጓዝ ትልቅ እገዛ በማድረግ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *