በዓለም አቀፍ ደረጃ በየ ‘43’ ሰከንድ አንድ ህጻን በሳምባ ምች ምክንያት ህይወቱን ያጣል፡፡

የዓለም አቀፍ የሳምባ ምች እና ከመወለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ህፃናት በማሰብ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ “ከመወለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ህፃናት የወላጅ እቅፍ ፍቱን መድሀኒት ነው” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል::

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው የሳምባ ምች ከአምስት አመት በታች ያሉ ህፃናት ዋና ገዳይ በሽታ መሆኑ ሲሆን በአለም በየ43 ሰከንድ የአንድ ህፃን ህይወት እንደሚያልፍ ተነግሯል፡፡

ይህ “ትኩረት የተነፈገው” በሽታ ከየትኛውም በሽታ በላይ ለበርካታ ህፃናት ሞት ምክንያት መሆኑም ተጠቁሟል::
በዚህም በሽታ ህይወታቸውን የሚያጡ ህፃናት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ህብረተሰቦች ውስጥ የሚገኙ፣ የክትባት አገልግሎት ዝቅተኛ በሆነባቸው እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ባለባቸው አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ህፃናት ይበልጥ ለበሽታው ተጋለጭ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

ከአጠቃላይ የሞት ምጣኔ 17 በመቶ የሳምባ ምች የሚይዝ ሲሆን በአመት ከ36 ሽህ በላይ እንደ ማለት ነው፤ይህም በቀን ከመቶ ህፃናት በላይ በሳምባ ምች በሽታ ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ ያሳያል፡፡

በኢትዮጵያ በ2003 ዓ.ም የሳምባ ምች በሽታን መርምሮ ፍቱን በሆነ ፀረ ባክቴሪያ የማከም አገልግሎት በማህበረሰብ ተደራሽ ቢሆንም፣ የህከምና አገልግሎት ተጠቃሚ ህፃናት ቁጥር በእጅጉ ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል::

እንዲሁም ከመወለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ህፃናት ቀን በአለም አቀፍ ለ12ኛ በኢትዮጲያ ለ9ኛ ጊዜ ከመወለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ህፃናት “የወላጅ እቅፍ ፍቱን ህክምና ነው” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በኢትዮጵያ በአመት 27,600 የሚሆኑ ህፃናት በቀላል እና ከፍተኛ ወጪ በማይጠይቅ ህክምና የአንድ ወር እድሜ ሳይሞሉ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ነው የተገለጸው፡፡

በአሁኑ ወቅት ከመወለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ጨቅላ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከሰተው የሞት ምጣኔ ከ 5 አመት በታች ላሉ ሕፃናት ሞት ከፍተኛውን እንደያዘም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በእለኒ ግዛቸው
ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.