ኢትዮ ቴሌኮም እና ሴኔት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ቴሌ ብርንና ሲኔት ሶፈትዌርን በማስተሳሰር የአገልግሎትና የግብይት ክፍያዎችን በቴ ብር ለመፈጸም የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አደረጉ።

ይህም አሰራር ቴሌ ብርና ሲኔት ሶፈተዌርን በማስተሳሰር የሲኔት ሶፍትዌር ተጠቃሚ አጋሮች ደንበኞቻቸው ግብይት ሲያከናውኑ ቀላል፣ ፈጣን ምቹና አስተማማኝ የሆነውን የዘመነን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብርን ተጠቅመው የአገልግሎት ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

በተለይም ይህ አሰራር የሲኔት ሶፍትዌርን በመጠቀም አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች፣ ፋርማሊዎች፣ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች ካፌዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች’ የመዝናኛና የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋማት ደንበኞቻቸው ከ25 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ ደንበኞች ያሉትን ቴሌብርን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የአገልግሎት እና የግብይት ክፍያዎቻቸውን እንዲያከናወነ ይረዳቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በዚህም መሰረት ደንበኞች ለአገልግሎት ወይም ግብይት ክፍያዎችን ለመፈጸም የአገልግሎት ሰጪውን ተቋም ድርጅት ኬው አር ኮድ (QR Code ) በማንሳት (Scan ) እንዲሁም በቅድሚያ ከፍያቸውን በቴሌብር እንደሚከፍሉ በማሳወቅ በሞባይል ስልካቸው በሚደርሳቸው የክፍያ የሚስጥር ቁጥር ስሂሳብ ባለሙያውች በመናገር ክፍያቸውን በቴሌብር መተግበሪያ ወይም አጭር ቁጥር (USSD) ሲፈፅሙ ከ127 የክፍያ ማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደሚደርሳቸዉ በማብራሪያዉ ላይ ተነስቷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌብር መላ – የግለሰብ ደንበኞች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ወኪሎች የአነስተኛ ብድር አገልግሎት በቴሌብር አካውንታቸው አማካኝነት የሚያገኙበት፣ ቴሌብር እንደኪስ የቴሌብር ደንበኞች በአካውንታቸው ላይ ያላቸው ቀሪ የሃሳብ መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ የሚጠቀሙት እንዲሁም #ቴሌብር ሳንዱቅ – ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለደ መጠን የሚታሰብባቸው የቁጠባ ዓይነቶችን የሚጠቀሙበት ሲሆን አገልግሎቶቹን ከዳሽን ባንክ ጋር በአጋርነት ፋይናንስ ለሁሉም በሚል መርህ በማቅረብ የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

ኩባንያው በቴሌብር አገልግሎት እስከ አሁን ከ153 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ማስተናገድ እንደቻለም ታውቋል፡፡

በየውልሰዉ ገዝሙ
ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.