ኦሊሴንጎ አባሳንጆ መቐለ ገቡ፡፡

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንትና በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ኦሊሴንጎ አባሳንጆ በዛሬው ዕለት መቐለ ገብተዋል።

ከፍተኛ ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ታውቋል።

ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት መምራታቸው ይታወቃል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.