በመሬት ላይ ሲደረግ በቆየ የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ37 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ዝርፍያ ጋር በተያያዘ ሲያደርገው በቆየው የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ፤የክፍለ ከተማ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች ፤ ባለሙያዎች ፤ ደላሎችና ከህብረተሰቡ በድርጊት የተሳተፉትን ጨምሮ 37 ሰዎችን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ቀሪዎቹን ግለሰቦችም ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው እንደሚገኝ የተመላከተ ሲሆን ተጨማሪ የማጥራት ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል::
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችም:-
- ለምለም አባይነህ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፃሚ
- አቶ ከፍያለው አሰፋ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
- አቶ ዋሲሁን ሰውነት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
- አቶ ኢብራሂም ሀሰን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
- አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
- አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ
- አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ
ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች - አቶ አየለ ጉቱ
- አቶ ጎሳዬ ደሜ
- አቶ በፍቃዱ ወንደሰን
- አቶ ሮባ ደበሌ
- አቶ መታሰቢያ አባተ ናቸው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም











