በኢትዮጵያ በኤች አይቪ ከሚያዙ ዜጎች መካከል 69 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተባለ፡፡

በየአመቱ እድሜያቸው ከ15-24 ባሉ የማህበረሰብ ክፍልም አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት መካከል ሴቶች 69 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ድኤታ አማካሪ አቶ ፍቃዱ ያደታ በሀገር አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ብዙዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የማህበረሰብ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡

በሀገራችን በልጃገረድ እና ወጣት ሴቶች የኤችአይቪ ስርጭት መጠን 0.4 በመቶ እንደሆነ መረጃዎች ቢገልፁም በ2021 እድሜያቸው ከ15-29 ዓመት ያሉ ወጣት ሴቶች በአጠቃላይ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል 34 በመቶውን ይይዛሉ ነው የተባለው፡፡

ይህ ቁጥር ይፋ የሆነው የጤና ሚኒስቴር ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እና ከኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የአለም ኤድስ ቀን ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

የኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያ ካንትሪ ፕሮግራም ማኔጀር ዶክተር መንግስቱ ገ/ሚካኤል በተሰበሰበ መረጃ በሀገራችን ባለፈው ዓመት 1.5 ሚሊየን ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ይህም ከታሰበው እና ከተገመተው በ 3 ዕጥፍ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ባለፈው አመት የተገመተው ወደ 5 መቶ ሰው በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ቢሆንም ግን በ3 ዕጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ብዙዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የማህበረሰብ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ያሉት የጤና ሚኒስቴር ድኤታ አማካሪ አቶ ፍቃዱ ያደታ ናቸው።

በየአመቱ እድሜያቸው ከ15-24 ባሉ የማህበረሰብ ክፍልም አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት መካከል ሴቶች 69 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚወስዱም ገልጸዋል ።

በሀገራችን በልጃገረድ እና ወጣት ሴቶች የኤችአይቪ ስርጭት መጠን 0.4 በመቶ እንደሆነ መረጃዎች ቢገልፁም በ2021 እድሜያቸው ከ15-29 ዓመት ያሉ ወጣት ሴቶች በአጠቃላይ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል 34 በመቶውን ይይዛሉ ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በፊት ከነበረው አሁን ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር “በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረ ነው ” ያሉት አማካሪው በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገ ጥናት ይፋ በሆነ መረጃ እድሜያቸው ከ15-29 ባሉ ሴቶች ቫይረሱ ” አስደንጋጭ ” በሆነ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል ።

ዕድሜያቸው ከ15-24 ባሉ ወጣቶች በወንዶች 39 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ስለ ቫይረሱ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች የተሟላ እውቀት ሲኖራቸው በሴቶች ደግሞ 24 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ስለ በሽታው ዕውቀት አላቸው።

የአለም ኤድስ ቀን “ፍትሃዊና ተደራሽ የኤችአይቪ ኤድስ አገልግሎት ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

በእስከዳር ግርማ
ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *