የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአንዳንድ ወገኖች አጀንዳ ይቀርብለት እንደነበር አስታወቀ

ኮሚሽኑ ገለልተኛ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ወገኖች አጀንዳ የመስጠት እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ አስታውቋል።
እንዲሁም ለኮሚሽኑ አወያዮችና አመቻቾች ስልጠና ካልሰጠን የሚሉ አካላት ስለመኖራቸውም ተነስቷል።

እነዚህ እንቅስቃሴዎች ደግሞ በህዝቡ ዘንድ ብዥታን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ከዚህ ባለፈም በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ወደ አካባቢው ተዘዋውሮ መስራት እንዳልቻለም ገልጿል።

እነዚህም በኮሚሽኑ የስራ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ሆነዋል ተብሏል።
ነገር ግን ኮሚሽኑ አጀንዳ የሚሰጡ አካላት እነማን እንደሆኑ ከመግለፅ ተቆጥቧል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።

በአባቱ መረቀ
ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.