በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ።

ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባት ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ተወሰነ።

የቅጣት ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ በጥቅምት 15 ቀንፐ 2015 ዓ/ም የወንጀል ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።

ተከሳሿ ክሱ ከደረሳት በኋላ ጠበቃ የማቆም አቅም እንደሌላት መግለጿን

ተከትሎ በፍርድ ቤቱ በመንግስት ተከላካይ ጠበቃ የህግ ድጋፍ ተደርጎላታል።

ክሱ በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ ተከሳሿ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ስትል የሰጠችውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ በጥቅምት 30 ቀን በነበረ ቀጠሮ ዓቃቢህግ የሟች ግዮናዊት እና ክርስቲና መላኩ ወላጆችን ጨምሮ ስድስት ምስክሮችን አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን እንደሰጠ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች፡፡

የምስክር ቃል የመረመረው ችሎት በህዳር 13 ቀን በነበረ ቀጠሮ ተከሳሿ በተሰሰችበት ወንጀል እንድትከላከል ብይን ሰየሰጠ ቢሆንም ተከሳሿ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ገልጻለች።

ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ በፖሊስ ጣቢያ የሰጠችውን የዕምነት ቃል በመያዝና የዓቃቢህግ የሰው ምስክሮችን ቃል መርምሮ በተከሰሰችበት ተደራራቢ ወንጀል የጥፋተኛ ፍርድ አስተላልፎባታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.