የአፍሪካ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ሊጀመር ነው

ኢትዮጵያን ጨምሮ 17 አገሮች የአፍሪካ አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ገበያን በሙከራ ደረጃ ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ፡፡
ገበያው ንብረትነታቸው ሙሉ በሙሉ አፍሪካዊ የሆኑ አየር መንገዶች ከአንዱ አገር ወደ ሌላው በሚያደርጉት በረራ የነበሩባቸውን ገደቦች የሚያስቀር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስታዉቋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ እና ሌሎች አስራ ስድስት አገሮች የአፍሪካ አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ገበያን በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

በሥምምነቱ መሠረትም አስራ ሰባቱ አገሮች ገበያቸውን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ አንዳቸው ለሌላቸው ይከፍታሉ የተባለ ሲሆን፤ ይህ ገበያም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መልካም ዕድል ይዞ የሚመጣ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ገበያው በሙከራ ደረጃ መተግበር መጀመሩ ይፋ የሆነው ባለፈው ጥቅምት 25 ቀን 2015 በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር በተካሔደ መርሐ-ግብር ላይ ነበር።
ይህን የሙከራ ገበያ ለመጀመር ከተስማሙ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ኬፕ ቬርዴ፣ ኮት ዲቯር፣ ካሜሩን፣ ጋና እና ኬንያ እንደሚገኙበት ዶቼ ቬሌ ዘግቧል።

የአፍሪካ አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መሠረት፣ የአህጉሪቱን የአየር ማጓጓዣ ዘርፍ ለውድድር ክፍት ለማድረግ፣ ከ23 ዓመታት ገደማ በፊት የተፈረመው በካሜሮኗ ዋና ከተማ ያማሱክሮ ሥምምነት ነበር፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.