በኦሮሚያ ክልል ‘እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች’ እየተፈጸሙ እንደሆነ ኢሰመኮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ ዞኖች በተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን በአምስት ወር ግምገማው ነው ኢሰመኮ የገለጸው።

ኢሰመኮ በርካቶች የተቀጠፉበትን የሰሞኑን ጥቃት ጨምሮ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2015 ዓ.ም የደረሱ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስለተፈናቀሉባቸው ግጭቶች እና ጥቃት ዙሪያ ሪፖርት አውጥቷል።

በእነዚህ ዞኖች ከሰላማዊ ነዋሪዎች በተጨማሪ የመንግሥት የፀጥታ እና የአስተዳደር አባላት መገደላቸውን፣ የመንግሥት እና የሲቪል ሰዎች ንብረቶች መዘረፋቸውን እንዲሁም ወድማቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም መሠረተ ልማቶች እና አገልግሎቶች መውደማቸውን ገልጾ ነዋሪዎች ከእነዚህ አገልግሎቶች ውጪ መሆናቸውን ኢሰመኮ አስፍሯል።

በጥቃቶቹ እና በግጭቶቹ ሳቢያ የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ያለ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ፈታኝ እና አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ኑሯቸውን እንዲገፉ ተደርገዋል ብሏል።

በስድስት ወራት የደረሱትን ግጭቶችና ጥቃቶች ያስከተሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በመገምገም፣ በሰብዓዊ መብቶች መርሆችና ድንጋጌዎች መሠረት እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተብለው የሚመደቡ መሆናቸው በርካታ አመላካቾች አሉ ብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.