አስደናቂው የካታር የአለም ዋንጫ ከ32ቱ ሩቡ ሲቀሩ በጨዋታው ከመዘንነው ከ64/56ቱ ነጉዷል ዛሬ እና ነገም አራት ይቀራሉ::

የሩቅ ምስራቆቹን ኮሪያና ጃፓንን ያሰናበቱት ክሮሺያና ብራዚል በኢዱኬሽን ሲቲ ይጋጠማሉ

በምድቧ እንደተገመተው ያላስደመመችን ፌቨራይቷ ሴሌሳኦ በመጀመሪያው ጥሎ ማለፍ በውድድሩ ካስቆጠረችው ጎሎች የላቁ ለማስቆጠር ከግማሽ ስአት ብዙም ያልበለጠ ነው የወሰደባት እንዲሁም ብርቅ ልጇን አስመልሳ አበርክቶቱ በሚገባ አንጸባርቋል በ16ቱ ጥሎ ማለፍ በጎል የተንበሸበሸችው ሴሌሳኦ በኢዱኬሽን ሲቲ ክሮሺያን ትፋለማለች ::

በአንጻሩ አገር ሆና ከተመሰረተች ሩብ ክፍለዘመን በቅጡ ያልሞላት እንጭጭ አገር በእግር ኳሱ መድረክ ከአቅሟ በላይ በመሰንዘር የአባት ዩጎዝላቪያን ሌጋሲ ያስቀጠለች ብቸኛ ወራሽ መስላለች ዳቮር ሱከር ያነሳው ዱላ በነ ዳዶ ፕርሶ በኩል አልፎ እነ ዳሪዮ ስርና ለነ ትንሹ ሉካ አሻግረዋል እድሜው በጨመረ ቁጥር እንደ ወይን እየጣፈጠ የመጣው ሉካ የታላላቆቹን አደራ ተረክቦ በራሺያ ቡድኑን ለፍጻሜው አብቅቷል አሁን በአንጋፋ ተጫዋቾች ያንን መደገም ቢከብድም ልምድ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ከጃፓን በነበረው ጨዋታ አሳይተውናል ዛሬ ግን ከፊታቸው የተጋረጠችው የውድድሩ ምልክት የደቡብ አሜሪካዋን ታላቅ መደርመስ ግድ ይላቸዋል ይሳካ ይሆን ከ11:00 ጀምሮ ጠብቁን::

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *