ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በበጀት አመቱ ከ1.7 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን ገለፀ።

ባንኩ በበጀት አመቱ ከግብር በፊት 1.76 ቢሊየን ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ካለፈው የበጀት አመት ጋር ሲነፃፀር ከ139 ሚሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ባንኩ ገልጿል።
የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ6.22 ቢሊዮን ወይም የ14 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 49.76 ቢሊዮን መድረሱ ባንኩ አሳውቋል።

ባንኩ በበጀት አመቱ ካስመዘገበው አበረታች የፋይናንስ እንቅስቃሴ እና ውጤት ባሻገር ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከውኛለሁ ብሏል።
ከነዚህም አንዱ ተወዳዳሪነትን እና የባለአክስዮኖችን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ስትራቴጂካዊ እቅዱን በመከለስ ወደ ስራ ገብቷል።
ባንኩ ለረጅም አመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የኮር ባንኪንግ ሲስተም ወደ ተሻለ እና የቅርብ ጊዜ ስሪት ወደሆነው T24 version 2020 የማሳደግ ስራውን አጠናቆ ወደ ተግባር ገብቷል ተብሏል።

ይህም አሰራር የባንኩን ዋና ዋና የስራ ሂደቶችን በማቀላጠፈ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ነው የተባለው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ኢ-ብር ከሚባል ኩባንያ ጋር በመተባበር “NIB E-Birr” የሞባይል ዋሌት እና የኤጄንሲ ባንኪንግ አገልግሎቶችን በማቅረብ የዲጂታል የንግድ ልውውጡን አዘምኗል።

በ717 መስራች አባላት የተጀመረው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዛሬ ላይ ከ5 ሺ 5 መቶ በላይ መድረሱ ተገልጿል።
ባንኩ በዛሬው እለት የባላክሲዮኖች 23ተኛ መደበኛ እና 19ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

በመሳይ ገ/መድህን
ታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.