የወረቀት ህትመት እና ማሸጊያ ቴክኖሎጂ ግብዓቶች እና መፍትሄዎች ዓለም ዓቀፍ አውደርዕይ ሊዘጋጅ ነው።

አፍሪ ፕሪንት እና ፓኬጂንግ ኤክስፖ የወረቀት ህትመት እና ማሸጊያ ቴክኖሎጂ ግብዓቶች እና መፍትሄዎች ዓለም ዓቀፍ አውደርዕይ ለሰባተኛ ጊዜ ሊዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል።

ከወረቀት እና ህትመት ማሸጊያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ ጎን ለጎን በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ነው የተባለው የሳይን እና ግራፊክስ ኤክስፖም ይካሄዳል ተብሏል።

የኤክስፖው አዘጋጅ የሆነው ፕራና ኤቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነብዩ ለማ “አገራችን በ14.4 በመቶ አመታዊ እድገት የህትመት እና የወረቀት ቴክኖሎጂ በማስገባት ከአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አገር ናት” ብለዋል።

የአፍሪ ፕሪንት እና ፓኬጂንግ እንዲሁም የሳይን እና ግራፊክስ ኤክስፖ መካሄድ ለተሳታፊ ኩባንያዎች ደንበኞች ሊሆኑ ከሚችሉ ገዢዎች ጋር ለመገናኘት እና ንግዳቸውን ወደፊት ለማራመድ ጥሩ መድረክ እንደሚሆን አክለው ገልፀዋል።

ዝግጀቱ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ድጋፍ እንዲሁም በፓን አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (PACCI) እና የኢትዮጵያ አሳታሚዎች እና አታሚዎች ማህበር ተቋማዊ አጋርነት ይከናወናል ተብሏል።

ከታህሳስ 11-13/2015 ድረስ በስካይላይት ሆቴል በሚዘጋጀው በዚህ አውደ-ርዕይ ከ40 በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ሥራዎቻቸውን ያስተዋውቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ የንግድ ጎብኚዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *