6ተኛዉ ኦዳ አዋርድ የፊታችን ታህሳስ 18 በወደጃጅነት ፓርክ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

በዘንድሮዉ ኦዳ አዋርድ ከ60 በላይ እጩዎች ለአሸናፊነት ተለይተዉ ይሸለማሉ የተባሉ ሲሆን ሶስት ዘርፎች ማለትም በሙዚቃ፣በፊልም እና መፅሀፍ ዘርፎች ተሸላሚውች የቀረቡ ሲሆን የህይወት ዘመን ተሸላሚም የሚካተትበት ይሆናል ተብሏል።

በ2010 የተጀመረዉ እዳ አዋርድ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ20 በላይ በሆኑ ዘርፎች 300 ለሚሆኑ ባለሙያዎች የእዉቅና ሰርተፍኬት የዋንጫ ሽልማት ሰጥቻለዉ ብሏል።

በቀጣይ በሁሉም የሀገራችን ቋንቋዎች የሚሰሩ የኪነጥበብ ስራዎችን የኢትዮጵያ ሀገርኛ የኪነ ጥበብ ስራዎች በሚል ለማካተት የታሰበ መሆኑንም በመግለጫዉ ተገልጿል።

የዘንድሮው ሽልማት የሚቀርቡት እጩዎች በ2014 ዓ.ም ከመስከረም 1 እስከ ጷግሜ 5 የተሰሩ ብቻ እንደሚሆኑ በመግጫዉ የተገለፀ ሲሆን በኦሮምኛ፣በሀረሪ እና በቤንሻንጉል ከፍተኛ የኪነ ጥበብ ስራዎችን ያበረከቱ አንጋፋ ባለሙያዎች የህይወት ዘመን ተሸላሚ እንደሚሆኑ በመግለጫዉ ተገልጿል።

የ6ኛው ኦዳ አዋርድ የሽልማት ዘርፎች

በሙዚቃ

የአመቱ ምርጥ አልበም
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ
የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ስቱዲዮ
የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ
የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ጥምረት
የአመቱ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ
የመአቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት

በፊልም

የአመቱ ምርጥ ፊልም
የአመቱ ምርጥ ወንድ ተዋናይ
የአመቱ ምርጥ ሴት ተዋናይት
አመቱ ምርጥ ዳይሬክተር
የአመቱ ምርጥ ፊልም ድርሰት
አመቱ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር

በመፅሃፍ ዘርፍ

የአመቱ ምርጥ የልብወለድ መፅሃፍ
የአመቱ ምርጥ የግጥም መፅሃፍ

የህይወት ዘመን ተሸላሚ

በአፋን ኦሮሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ
በሀረሪኛ የህይወት ዘመን ተሸላሚ
በቤንሻንጉል የህይወት ዘመን ተሸላሚ የሚሆኑ ሲሆን የእዚህ አመት 6ኛው ኦዳ አዋርድ መታሰቢያነቱ ለአርቲስት አበበ ተሰማ እንደሆነ አዘጋጇ በሻቱ ቶለማርያም ተናግራለች።

በአቤል ደጀኔ
ታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.