የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2ኛውን ዙር የአገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ታሕሳስ 16 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ አሳሰበ፡፡

የ2ኛውን ዙር የአገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በታሕሳስ 16/2015 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ በዛሬው ዕለት አሳስቧል።

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታሕሳስ 18 እስከ ታሕሳስ 21 ቀን 2015 ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.