የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት የጋራ ኮሚቴ ለመሰየም ተስማሙ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ባለፈዉ ጥቅምት ማብቂያ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት ገቢራዊነት የሚቆጣጠር የጋራ ኮሚቴ ለመሰየም ተስማምተዋል ተብሏል።

የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ባለስጣናትና የጦር አዛዦች ከዚሕ ቀደም በተፈራረሙት የሰላም ስምምነት መሠረት የስምምነቱን ገቢራዊነት የሚከታተልና የሚቆጣጠር የጋራ ኮሚቴ ያዋቅራሉ።
ኮሚቴዉ ከሁለቱ ወገኖች፣ ከአፍሪቃ ሕብረትና ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን (IGAD) የሚወከሉ ባለስልጣናትና ባለሙያዎችን ያካትታል።

የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት የጦር አዛዦች ካለፈዉ ማክሰኞ እስከ ትናንት ማታ ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ ባደረጉት ስብሰባ ስለስምምነቱ የእስካሁን ገቢራዊነትና ሒደቱን ስለሚቆጣጠረዉ የጋራ ኮሚቴ አወቃቀር ተነጋግረዋል።

የጦር አዛዦቹ በዝግ ያደረጉትን ንግግር የመሩት የአፍሪካ ሕብረትና የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን አደራዳሪዎች እንዳስታወቁት ተሰብሳቢዎቹ የጋራ ኮሚቴዉን ኃላፊነትና ዉክልና በዝርዝር አዉስተዉ እንዲመሰረት ተስማምተዋል።

አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነሕ ገበየሁን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ኮሚቴዉ የሰላም ስምምነቱን ገቢራዊነት የመከታተል፣የመቆጣጠርና (ከአደጋ) የመከላከል ኃላፊነት አለበት።

የሚደርስበት ዉሳኔና የሚያቀርበዉ ዘገባም በሰላም ስምምነቱ ተፈራራሚና ባደራዳሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል።

የአፍሪቃ ሕብረት የሚሰይመዉ የባለሙያዎች ቡድን፣ ስምምነቱ በተለይም የተኩስ አቁም ዉሉ መከበር አለመከበሩን፣በስምምነቱ ያልተካተቱ ነገር ግን የጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ ኃይሎች ከየያዙት አካባቢ ለቀዉ መዉጣት አለመዉቸዉን እየተከታተለ ለጋራ ኮሚቴዉ ሙያዊ ዘገባ ያቀርባ፤ ድጋፍ ይሰጣልም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.