ገዳ ባንክ ከተመሠረተ ከ3 ዓመት በኋላ ስራ ጀመረ።

ከ1.1 ቢሊየን በላይ የተፈረመ ካፒታል ይዞ ነው ስራ የጀመረው ።

ገዳ ባንክ 552 ሚሊየን የተከፈለ እንዲሁም ከ1.1 ቢሊየን በላይ የተፈረመ ካፒታል ይዞ ከትናንት ታህሳስ 13 2015 ዓም ጀምሮ ስራ መጀመሩን ገልጿል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ባንኩ በ25 አደራጅ ኮሚቴ አባላት አስተባባሪነት ከ28ሺህ በላይ በሚደርሱ ባለአክሲዮኖች መመስረቱን ተናግረዋል።

በተደረገ ጥናት በአገራችን ያለው የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት ከ50 በመቶ በታች ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለይም የገጠሩን ክፍለ ኢኮኖሚ ከባንክ ተደራሽነት እና በቂ የባንክ አገልግሎት ጋር በማገናኘት ያለውን ክፍተት ለመሙላት አቅዶ መነሳቱን ገልፀዋል።

የባንኩ የአክሲዮን ባለቤቶች ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት ባልደረሰባቸው አከባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ቁጥር በሆነ የአክሲዮን ባለቤት ቁጥር የተቋቋመ መሆኑም ተነግሯል።

ገዳ ባንክ በመጀመሪያ ዙር በያዝነው የፈረንጆች 2022 አመት ማለቂያ ድረስ በሚከፈቱ ከ30 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎቹ ስራ እንደሚጀምርም ተገልጿል።

ባንኩ ከተለያዩ አለምአቀፍ ባንኮች ጋር ግንኙነት መፍጠሩም የተገለፀ ሲሆን ቴክኖሎጂ ተኮር የሆነ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱም ነው የተነገረው።

ገዳ ባንክ መፈክሩን” የአዲሱ ትውልድ ባንክ” በሚል ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ልክ በዛሬው ዕለት ነበር ምስረታውን ያካሄደው።

ታህሳስ 15 2015 በይፋ ስራ ለመጀመር የምርቃት ስነስርዓቱን የሚያካሂድ ይሆናል።

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.