የተጀመረው የሰላም እንቅስቃሴ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል ….. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የጠንካራ ዲፕሎማሲ ስራ መሠረቱ ጠንካራ ውስጣዊ ሁኔታ መሆኑን ገልጸዋል።

እየተካሄደ ባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራሮች እና የሚሽን መሪዎች ውይይት ላይ ይህ ጉዳይ በአጽንኦት መነሳቱን ጠቁመዋል።

በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅሰው፥ በሌሎች አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም ተጠያቂነት የማረጋገጡ ጉዳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 18ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.