ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቅ አብንን በሚመለከት አልሰጥም ያለውን እውቅና መቀለበሱን ገለጸ፡፡

ምርጫ ቦርድ አብን የካቲት 14 እና 15 ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ለተመረጡት የፓርቲው አመራሮችና ጉባዔው ላሳለፋቸው ውሳኔዎች እንዲሁም ለውሳኔዎቹ ውጤቶች እውቅና አልሰጥም በማለት ሰሞኑን ያሳለፈውን ውሳኔ መቀልበሱን አስታውቋል።

ቦርዱ የፓርቲውን ሕልውና ለማስቀጠልና ፓርቲው ሲያከናውናቸው የቆዩ ተግባራት ዋጋ አልባ እንዳይሆኑ በማሰብ ውሳኔውን መቀየሩን መግለጹን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግባለች።

ቦርዱ ውሳኔውን የቀየረው፣ ፓርቲው የቦርዱ ውሳኔ አግባብነት የለውም በማለት ጉዳዩን እንደገና መርምሮ የእርምት ውሳኔ እንዲሰጥለት መጠየቁን ተከትሎ መሆኑን ጠቅሷል። ቦርዱ የፓርቲውን ጉባኤ ውድቅ ያደረገው፣ በፓርቲው ሕግ መሠረት አልተከናወነም በማለት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.