ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ በቁልቢ እና በሐዋሳ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአመት ሁለት ጊዜ በታኅሣሥ እና በሐምሌ 19 በድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ዘንድሮም በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እተከበረ ነው የሚገኘው፡፡

በቁልቢ በመከበር ላይ በሚገኘው የንግስ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

በዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች በድምቀት እየተከበረ ሲሆን፤ የክብረ በዓሉን ድምቀት ለመመልከት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ጎብኚዎችም በስፍራው መገኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.