ኡሁሩ ኬንያታና ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ መቀሌ ገቡ፡፡

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት እና የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎች በሰላም ስምምነቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አካላት ዛሬ መቀሌ ገብተዋል።

መቀሌ ከተማ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

መቀሌ የገቡት የእንግሊዝ አምባሳደርን ጨምሮ ወደ 32 የሚሆኑ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና ወታደራዊ አመራሮች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.