“የቱ ጋር ነህ “የተሰኘው የድምፃዊ ዲበኩሉ ታፈሰ የመጀመሪያው አልበም ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓም ለአድማጭ ሊያደርስ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም በጃኖ ባንድ የሚታወቀው አርቲስቱ አልበሙን ከኬኔቲክ ዳውን ጋር በመሆን መስራቱን የተናገረ ሲሆን ፤ ትላልቅ የሙዚቃ ባለሞያዎች በግጥም እና በዜማ ተሳትፈዋል ብሏል።
ከባለሞያዎቹም መካከል ይልማ ገብረአብ ፣ ልጅ ማይክ እንዲሁም አርቲስቱም በግጥም መሳተፉን ተናግሯል።
አልበሙ 13 የሙዚቃ ስራዎች የተካተቱበት ሲሆን በቅርቡ አንድ ቪዲዮ ለአድማጭ መድረሱን ተጠቁሟል።
የአልበሙ ስያሜ ሰዎች ያሉበትን እና የነበሩበትን እንዲመለከቱ በማሰብ “የቱ ጋር ነህ?” ሲል መጠሪያ እንደተሰጠው ድምጻዊው ተናግሯል።
በእሌኒ ግዛቸው
ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም











