“ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ” መጽሐፍ ዛሬ ተመርቋል።

መጽሐፉ የ28 ወጣት ፖለቲከኞች ፤ማህበራዊ አንቂዎች ፤ምሁራንና ህዝብን በማሳተፍ በጋዜጠኛ ሊዲያ አበበ እና በጋዜጠኛ ሱራፌል ዘላለም የተዘጋጀ ነው ።

“ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ፤ ለመቀራመት ወይስ የማዳን ተልዕኮ የተሰኘውና የፖለቲካ ይዘት ያለው መፅሐፍ በርካታ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ያለፍንባቸውን ” የፖለቲካ ሂደትን የሚያስቀኝ ፤ዛሬ ያለንባቸውን የፖለቲካ ቅርቃሮችን የሚያስረዳ እና የመፍትሔ ሃሳቦችን እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል ።

182 ገፆች ያሉት ይህ መፅሃፍ ሃገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በሃይል እየተፈተነች ስላለችበት እና ህብረብሔራዊ አንድነቷን እየፈተናት የሚገኙ ጉዳዮችን በስፋት ያስረዳል ተብሏል።

የምኩራቡ ተቃርኖ ሃገርን ከጥፋት ለማዳን ያለመ ከሆነ በሃሳብ ተቃርኖ በምክኒያታዊነት መሞገት ሰብሃዊነት እና ሃገርን የሚበጃት መሆኑ ተገልጿል።

በመሳይ ገ/ መድህን

ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *