ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪክ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ሆኗል።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን አል-ናስር የእግር ኳስ ክለብን ተቀላቅሏል።
ሮናልዶ “በተለየ ሊግ እና ሀገር ውስጥ አዲስ ልምድ ለማግኘት ጓጉቻለሁ” ብሏል።
ሮናልዶ ከሳዑዲ አረቢያው አል-ናስር ጋር ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ውል መፈራረሙም ይፋ ሆኗል።
ሮናዶ በአል ናስር ቆይታው በዓመት 170 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም በእግር ኳስ ታሪክ የዓለማችን ውዱ ተከፋይ ያደርገዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም











