ብራዚል ከሳምንታት በፊት ባካሄደችው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሉላ ዳ ሲልቫ ማሸነፋቸውን ማሳወቋ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ ቦልሶናሮ እና ደጋፊዎቻቸው የምርጫው ውጤት ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸውም አይዘነጋም፡፡
ዛሬ ዳሲልቫ ለብራዚል ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት የሚያደርጋቸውን ቃለ-ማሃላ ፈፀመዋል፡፡

ከሰሞኑ ፔሌን ያጣችው ብራዚል የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ማወጇ የሚታወስ ቢሆንም የሉላ ዳሲልቫ በዓለ ሲመት በደመቀ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡
የአንጋፋው የእግር ኳስ ጭበበኛ ፔሌ የቀብር ስርዓቱ ላይ ዳሲልቫ እንደሚገኙም ይጠበቃል፡፡
በአብዱሰላም አንሳር
ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም











