ይህ የተገለጸው የማዕድን ሚኒስቴር ከክልል ማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የስድስት ወር አፈጻጸምን በተመለከተ ባደረገው ውይይት ላይ ነው፡፡
በውይይቱም ባለፉት ስድስት ወራት የነበረውን አጠቃላይ የማዕድን ምርት እና ያጋጠሙ ችግሮች ተነስተዋል።
በዚህ ውይይት ላይ እንደተገለጸው በተለይም የወርቅ ምርት በየጊዜው እያደገ የሚገኝ ቢሆንም እየታየ ያለው ህገወጥ ንግድ ግን ለዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ ፈተና መሆኑን እና ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።
በዘርፉ ያለው ኢንቨስትመንት ፍላጎቱ በየጊዜው እያደገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ይህም የማዕድን ምርቱን በከፍተኛ ደረጃ የመጨመር አቅም ያለው መሆኑ ተነስቷል።

የሲሚንቶ ምርትን በተመለከተ መንግስት የግብይት ስርአቱን የተለያዩ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑ ተጠቅሶ የፋብሪካዎችን የምርት አቅም ለመጨመርም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል።
ከስራ ውጪ ሆኖ የቆየውን መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን አዳዲስ ለሚገነቡ የሲሚንቶ ፋሪካዎች ክልሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱን የማዕድናን ሚንስቴር አስታውቋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዪጵያዊያን
ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም











