ዋዜማ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

አዘጋጁ ጆርካ ኤቨንት በዋዜማዉ ዕለት የሀገር ዉስጥና ኤርትራዊ ዘፋኞችን አጣምሬ ደማቅ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ስራዬን አጠናቅቂያለሁ ብሏል።

12 ቀናትን ሲካሄድ ከነበረዉን ባዛር በተጨማሪ አርብ ዕለት በዋዜማዉ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ ተወዳጅ ድምጻዊያንን እንደ ፍቅረ አዲስ ነቃ ጥበብ፣ሚካኤል በላይነህ እንዲሁም በኦሮምኛ ሙዚቃዎች እዉቅና ያገኘዉን ዮሳን ጌታሁን እና ከኤርትራ የመጣዉ ተወዳጅ ሙዚቀኛ ዳዊት ወ/ሰንበት በመያዝ ደማቅ የመዝግያ ኮንሰርት እንዳዘጋጀ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳዉቋል።

የዋዜማ ኮንሰርት የመግቢያ ትኬቱ በቴሌ ብር የሚሸጥ ሲሆን መደበኛ መግቢያ 300 ብር VIP ደግሞ 900 መሆኑ ታውቋል።

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.