የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከ4ሺህ በላይ ከብት ለማረድ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታክልቲ ከ3ሺህ በላይ ከብት እና ከ1ሺህ በላይ በግ እና ፍየል ለማረድ ድርጅቱ አስፈላጊዉን ቅድመዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በከብቶች ላይ ቅድመ እና ድህረ እርድ ምርመራዎችን በማከናወን የህብረተሰቡን ጤና እና ደህንነት በመጠበቅ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡
በቅድመ እርድ ምርመራዎች የታመሙ እንስሳትን ከመለየት በተጨማሪ፣ ለእርባታ የሚያገለግሉ እንስሳትን የመለየት ስራ የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በድህረ እርድ ምርመራዎች ደግሞ እንስሳቱ ያለባቸዉን በሽታ ወደ ሰዎች እንዳያስተላልፉ የሚረዳ ሲሆን፣ ባለፉት አምስት ወራት 35 ከብት እና 170 በግ በድህረ እርድ ምርመራ እንዲወገዱ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ስርጭቱን ለማቀላጠፍም ቅድመ-ዝግጅት ተደርጓል ያለዉ ቄራዎች ድርጅት፣ የተሽከርካሪ ጥገናዎችን እና ሰራተኛ ምድብ መካሄዱንም ገልጿል፡፡

ህብረተሰባችን ከህገወጥ እርድ እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ያሉት አቶ አታድልቲ ገ/ሚካዔል፣ በህገወጥ እርድ ምክንያት ከተማ አስተዳደሩ ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ማጣቱን ተናግረዋል፡፡

ህገወጥ እርድ የጤና ችግሮችን እና የኢኮኖሚ መዘዝ ከማምጣቱም ባሻገር፣ የአካባቢ ብክለት ማስከተሉ እና የእንስሳትን ምርታማነት አደጋ ላይ በመጣል በርካታ ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ድርጅቱ ከህብረተሰቡ የሚቀርበዉን የእርድ ጥያቄ በበአሉ እለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡

በአብድልሰላ አንሳር
ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *