ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በህገ-ወጦች እየተወረሩ ነው ተባለ፡፡

በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሽፈራው ናቸው፡፡

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች እየተወረሩ መሆኑን፣ በታችኛው ዕርከን የሚገኙ አመራሮችም የግብር ደረሰኝ እየሰጧቸው ያላግባብ ቦታዎቹ እየተሰጡ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቤቶች ልማት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት የሚውሉ ቦታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች መበራከታቸውም ታውቋል፡፡

ቦታዎቹን በሕገወጥ መንገድ ወስደው በክረምት ወቅት ጤፍ የሚዘሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የፍትሕ ቢሮው በጉዳዩ ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ አለበት ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ለአብነትም በአያት አካባቢ 10,000 ካሬ ሜትር ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸው መነገሩን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን የሚያስተዳድረው አካል ይዞታው በሥሩ እንደሚገኝ የሚገልጽ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ማስረጃው በሌለበት ግን ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ እውነታው ሌላ ሆኖ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ፍርድ ቤቶች በተቃራኒው የሚፈርዱበት ሁኔታ እንዳለም ተመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.