የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን 5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት እያሠራጨ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአገር ውስጥ የሚታየውን የዘይት ምርት ዋጋ ንረትና አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በመንግሥት በተላለፈው ውሳኔ ከተገዛው ውስጥ የ5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት ሥርጭት እያከናወነ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የምግብ ዘይት አምራች ኩባንያ በኮርፖሬሽኑ በኩል ተገዝቶ የቀረበው ይህ ምርት፤ ኮርፖሬሽኑ በአጠቃላይ ውል ከተፈራረመበት 21.5 ሚሊየን ሊትር የዘይት ምርት ከታኅሣሥ 21 ቀን 2015
ጀምሮ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የምርት ሥርጭት 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት በኮርፖሬሽኑ የምርት
ማከፋፈያ ማዕከላት አማካኝነት በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ጋምቤላ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከተሞች ተሠራጭቷል ብሏል፡፡

የዘይት ምርቱ መንግሥት ባወጣው የዋጋ ተመን መሠረት በሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበራትና በተፈቀደላቸው አቅራቢዎች አማካኝነት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በተላለፈው ኮታ መሰረት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ
ዋጋ እየቀረበ እንደሚገኝም ኮርፖሬሽኑ ተናግሯል፡፡

ቀሪው ዘይት በተከታታይ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የሚሰራጭ መሆኑንም የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጨምሮ ገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.